#Ethiopia #etok
ሙሉቀን መለሰ ከሸገር ታይምስ መፅሔት ጋር አድርጎት ከነበረው ቃለምልልስ የተቀነጨበ
ጋዜጠኛ፡- ለመሆኑ የምታደንቀው እና ለአንተ ጥሩ ምሳሌ የሆነህ ድምፃዊ ማነው
ሙሉቀን፡- እኔ በሀገራችን ከተፈጠሩ ድምፃውያን ውስጥ በጣም የማደንቀው በአንደኛ ደረጃ ምኒሊክ ወስናቸውን ሲሆን ከዚያ ቀጥሎ ተሾመ ምትኩን እና ማህሙድን ነው፡፡
ጋዜጠኛ፡- ጥላሁንን የረሳኸው መሰለኝ፡፡
ሙሉቀን፡- አልረሳሁትም፡፡ ጥላሁን ለእኔ ዘፋኝ አይደለም፡፡ ድምፅ እንጂ ታለንት የለውም፡፡ የመድረክ ብቃትም የሌለው ሰው ነው፡፡ እኔ ጥላሁን ገሠሠን እንደ ታላቅ አርቲስት ቆጥሬውም አላውቅም፤ አይደለም፡፡
ጋዜጠኛ፡- ሙሉቀን ምን ማለትህ ነው
ጥላሁን በሠላም ጊዜ ሕይወትን፣ ፍቅርን፣ ደስታና ኃዘንን በዜማው እና በዘፈኑ የገለፀ ድምፁ በሁሉም ዘንድ የተወደደ ዝነኛ እና ብቸኛ አርቲስት ነው ፡፡ ለዚህም የረጅም ጊዜ መልካም አገልግሎቱ ከተለያዩ ሽልማቶች አንስቶ የክብር ዶክትሬት እእስከማግኘት በቅቷል፡፡ ታዲያ አንተ አርቲስት አይደለም ብለህ ስትል ይኽን ታላቅ ሰው ማቃለል አይሆንም
ሙሉቀን፡- አየህ ስህተቱ የሚጀምረው እዚህ ጋ ነው፡፡ ሙዚቃ መስማት እና ማወቅ በጣም የተለያዩ ነገሮች ናችው፡፡ እናንተ ሙዚቃ በጆሯችሁ መስማት ነው የምታውቁት እኔ ደግሞ ሙዚቃን በደንብ መለየት እችላለሁ፡፡ ከዚህ ጋር አብሮ መታየት ያለበት ደግሞ የመድረክ አጠቃቀም እና ብቃት ነው።
ጋዜጠኛ፡- ምን ማለት ነው እስቲ ግልፅ አድርግልን
ሙሉቀን፡- አታቻኩለኛ!... ልነግርህ እኮ ነው! የመድረክ ብቃት ማለት አንድ አርቲስት በመድረክ ሲጫወት ከሚያጅቡት ሙዚቀኞች ጋር መናበብና መደማመጥ ከእነሱም ጋር ድምፁን አስማምቶ መጫወት ማለት ነው፡፡
ጋዜጠኛ፡- ታዲያ ጥላሁን በዚህ በኩል ችሎታ የለውም ነው የምትለኝ
ቅሬታስ ያሰማ የሙዚቃ አጃቢስ አለ
ሙሉቀን፡- አሁንም አላስጨረስከኝም! ጥላሁን የጉልበት ዘፋኝ ነው፡፡ ያቺ በተፈጥሮ የተሰጠችውን ድምፅ በጣም ስለሚኩራራባት አጃቢዎቹን በጣም ይንቃል:: በአብዛኛው ከሙዚቃ ውጭ ወደፊት ወይም ወደኋላ በመሄድ አጃቢዎቹን በጣም ያስጨንቃል ግራ ያጋባል፡፡ እሱ የሚያየው አፉን መክፈቱን ነው እንጂ የአጃቢ ሙዚቀኞቹን ምቾት አይጠብቅላቸውም፡፡ ይኼ ደግሞ ብዙ ጊዜ ስሞታ አስከትሎበታል፤ ግን የሚያዳምጥ የለም፡፡ ጥላሁን.. ጥላሁን ስለተባለ ብቻ ሁሉም ለእሱ ያደላል የአጃቢ ሙዚቀኞቹን ስሞታ የሚሰማ የለም፡፡ እነሱም ሥራችንን በዚህ ምክንያት እናጣለን በማለት እንደምንም እሱን ለመከተል ይገደዳሉ፡፡
ጋዜጠኛ፡- ለመሆኑ ከጥላሁን ጋር በሙያችሁ የነበራችሁ ግንኙነት እንዴት ነበር
ሙሉቀን፡- እንደ ማንኛውም ዘፋኝ አብሬው ሰርቻለሁ፡፡ ግን የመድረክ ብቃቱን አልወድለትም ነበር፡፡ መቼም ይኽንን በምልበት ጊዜ ብዙዎች ቅር እንደሚሰኙ ይገባኛል፡፡ ሁሉም እሱ ላይ የአምልኮ ወይም ካለሱ በስተቀር ግሩም ዘፋኝ የለም የሚል እምነት ሊኖራቸው ይችላል፡፡ እኔ ግን በሙያው ውስጥ ስለነበርኩ ያለምንም ይሉኝታ ነው ስለሁሉም የምናገረው፡፡ ስለዚህ አሁንም ደግሜ ጥላሁን ድምፅ እንጂ አርቲስት የሚለውን ሥም የሚያሟላ ታለንት የለውም የምለው፡፡ ደግሞም ትክክል ነኝ፡።
#Ethiopia #etok
ሙሉቀን መለሰ ከሸገር ታይምስ መፅሔት ጋር አድርጎት ከነበረው ቃለምልልስ የተቀነጨበ
ጋዜጠኛ፡- ለመሆኑ የምታደንቀው እና ለአንተ ጥሩ ምሳሌ የሆነህ ድምፃዊ ማነው?
ሙሉቀን፡- እኔ በሀገራችን ከተፈጠሩ ድምፃውያን ውስጥ በጣም የማደንቀው በአንደኛ ደረጃ ምኒሊክ ወስናቸውን ሲሆን ከዚያ ቀጥሎ ተሾመ ምትኩን እና ማህሙድን ነው፡፡
ጋዜጠኛ፡- ጥላሁንን የረሳኸው መሰለኝ፡፡
ሙሉቀን፡- አልረሳሁትም፡፡ ጥላሁን ለእኔ ዘፋኝ አይደለም፡፡ ድምፅ እንጂ ታለንት የለውም፡፡ የመድረክ ብቃትም የሌለው ሰው ነው፡፡ እኔ ጥላሁን ገሠሠን እንደ ታላቅ አርቲስት ቆጥሬውም አላውቅም፤ አይደለም፡፡
ጋዜጠኛ፡- ሙሉቀን ምን ማለትህ ነው? ጥላሁን በሠላም ጊዜ ሕይወትን፣ ፍቅርን፣ ደስታና ኃዘንን በዜማው እና በዘፈኑ የገለፀ ድምፁ በሁሉም ዘንድ የተወደደ ዝነኛ እና ብቸኛ አርቲስት ነው ፡፡ ለዚህም የረጅም ጊዜ መልካም አገልግሎቱ ከተለያዩ ሽልማቶች አንስቶ የክብር ዶክትሬት እእስከማግኘት በቅቷል፡፡ ታዲያ አንተ አርቲስት አይደለም ብለህ ስትል ይኽን ታላቅ ሰው ማቃለል አይሆንም?
ሙሉቀን፡- አየህ ስህተቱ የሚጀምረው እዚህ ጋ ነው፡፡ ሙዚቃ መስማት እና ማወቅ በጣም የተለያዩ ነገሮች ናችው፡፡ እናንተ ሙዚቃ በጆሯችሁ መስማት ነው የምታውቁት እኔ ደግሞ ሙዚቃን በደንብ መለየት እችላለሁ፡፡ ከዚህ ጋር አብሮ መታየት ያለበት ደግሞ የመድረክ አጠቃቀም እና ብቃት ነው።
ጋዜጠኛ፡- ምን ማለት ነው እስቲ ግልፅ አድርግልን?
ሙሉቀን፡- አታቻኩለኛ!... ልነግርህ እኮ ነው! የመድረክ ብቃት ማለት አንድ አርቲስት በመድረክ ሲጫወት ከሚያጅቡት ሙዚቀኞች ጋር መናበብና መደማመጥ ከእነሱም ጋር ድምፁን አስማምቶ መጫወት ማለት ነው፡፡
ጋዜጠኛ፡- ታዲያ ጥላሁን በዚህ በኩል ችሎታ የለውም ነው የምትለኝ? ቅሬታስ ያሰማ የሙዚቃ አጃቢስ አለ?
ሙሉቀን፡- አሁንም አላስጨረስከኝም! ጥላሁን የጉልበት ዘፋኝ ነው፡፡ ያቺ በተፈጥሮ የተሰጠችውን ድምፅ በጣም ስለሚኩራራባት አጃቢዎቹን በጣም ይንቃል:: በአብዛኛው ከሙዚቃ ውጭ ወደፊት ወይም ወደኋላ በመሄድ አጃቢዎቹን በጣም ያስጨንቃል ግራ ያጋባል፡፡ እሱ የሚያየው አፉን መክፈቱን ነው እንጂ የአጃቢ ሙዚቀኞቹን ምቾት አይጠብቅላቸውም፡፡ ይኼ ደግሞ ብዙ ጊዜ ስሞታ አስከትሎበታል፤ ግን የሚያዳምጥ የለም፡፡ ጥላሁን.. ጥላሁን ስለተባለ ብቻ ሁሉም ለእሱ ያደላል የአጃቢ ሙዚቀኞቹን ስሞታ የሚሰማ የለም፡፡ እነሱም ሥራችንን በዚህ ምክንያት እናጣለን በማለት እንደምንም እሱን ለመከተል ይገደዳሉ፡፡
ጋዜጠኛ፡- ለመሆኑ ከጥላሁን ጋር በሙያችሁ የነበራችሁ ግንኙነት እንዴት ነበር?